በዛሬው ዕለት በኤምባሲያችን በአይነቱ ልዩ የሆነ የምሰጋና እና ዕውቅና መርሐ-ግብር አካሂደናል። በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የስራ ባልደረቦች በስራቸው ላሳዩት ከፍተኛ ተነሳሽነት፣ የላቀ ውጤት እና በተለያዩ ጊዜያት ለቀረበላቸው አገራዊ ጥሪዎች ለሰጡት ፈጣን ምላሽ በአይነቱ ልዩ የሆኑ የምሰጋና እና ዕውቅና መርሐ ግብር ያካሄድን ሲሆን በዚህም ልዩ የምስክር ወረቀት ተሰቷቸዋል።
በዚሁ መድረክ ወደ ሚሲዮኑ ተመድበው ለመጡ አዲስ ዲፕሎማቶች ደማቅ አቀባበል ያደረግን ሲሆን በሚሲዮኑ የነበራቸውን ቆይታ በስኬት አጠናቀው ለሚመለሱ ዲፕሎማቶችም የምስጋና እና እውቅና መርሐ-ግብር ተካሂዷል። በመድረኩ በኬንያ የኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ኮሚኒት ማህበር አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው ዳያስፖራ አባላት ተገኝተዋል።
ዲፕሎማቶቼ በስራቸውን ላሳዩት ከፍተኛ ትነሳሽነት፣ ትጋት፣ ቁርጠኝነት፣ የላቀ ውጤት እንዲሁም በተለያዩ ጊዜያት ለቀረበላቸው አገራዊ ጥሪዎች ለሰጡት በጎ ምላሽ ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን እየገለፅኩ፣ ወደ ኤምባሲያችን አዲስ ተመድበው የመጡት ዲፕሎማቶች እንዲሁም የሥራ ቆይታቸውን ጨርሰው ለሚመለሱ ዲፕሎማቶች መልካም የስራ ዘመን እንድሆንላቸው እመኛለሁ።
Today, I had the distinct honor of convening a special ceremony to recognize and celebrate the exceptional dedication of the staff at the Ethiopian Embassy in Kenya. On this occasion, distinguished staff members were presented with special certificates in acknowledgment of their unwavering commitment, exemplary performance, and prompt responsiveness to national calls on various critical occasions.
During the same event, we had the great pleasure of warmly welcoming our newly assigned diplomats to the Mission. In parallel, a heartfelt appreciation and recognition program was held to honor our departing diplomats, who successfully completed their tenure at the Embassy. The event was graced by the presence of distinguished leaders of the Ethiopian community associations and esteemed members of the Ethiopian Diaspora residing in Kenya.
I wish to express my sincere and profound gratitude to all my diplomats for their sustained motivation, deep dedication, remarkable results, and their constructive response to the national calls made upon them at different times. I extend my best wishes for a rewarding and successful tenure to the newly assigned diplomats joining our Embassy, as well as to those returning home after the successful completion of their assignment.